ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የምጽዋ ወደብን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የምጽዋ ወደብን ጎበኙ
95
ምጽዋ ነሐሴ 30/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የምጽዋ ወደብን ጎበኙ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የቻይና አፍሪካ ጉባዔን አጠናቀው ዛሬ ማለዳ ወደ ኤርትራ ያቀኑ ሲሆን የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአሰብ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል። "መቀሌ" በሚል መጠሪያ የምትታወቀዋ የኢትዮጵያ መርከብ 11 ሺህ ቶን የሚመዝን የኤርትራ ዚንክ ከምጽዋ ወደብ ጭና ወደ ቻይና ታመራለች፡፡ የመርከቧ ጉዞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ስም ተሰይሟል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሰዓት በፊት አሰብ ወደብንና ከወደቡ እስከ ኢትዮጵያ ድንበር ያለውን 71 ኪሎሜትር መንገድ ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸውም በወደቡ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን አበረታተዋል፡፡ ሐምሌ መጀመሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ወደ ኤርትራ አቅንተው በሁለቱ አገሮች መካከል ላለፉት 20 ዓመታት ተቋርጦ የቆየውን ግንኙነት ለማስቀጠል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከፕሬዝዳንት ኢሳኢያስ ጋር መስማማታቸው ይታወሳል፡፡ ከስምምነቶች ውስጥም ወደብ መጠቀምን ጨምሮ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን መጀመር፣ ነጻ የዜጎች እንቅስቃሴና የአየር መንገዶች ስራ መጀመርን የተመለከቱ ስምምነቶች ይጠቀሳሉ፡፡