ሚኒስቴሩ በክልሉ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም የሚያግዝ የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ሚኒስቴሩ በክልሉ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም የሚያግዝ የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
57
አሶሳ ፤ መጋቢት 21/2014 (ኢዜአ ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከቄያቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የሚያግዝ የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።
በአሶሳ ተገኝተው ድጋፉን ዛሬ ያስረከቡት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ናቸው።
ድጋፉን የተረከቡት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን፤ ሚኒስቴሩ ላደረገው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ድጋፉ በክልሉ በግጭት የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀደመ ኑሯቸው በመመለስ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንደሚያጠናከር አስታውቀዋል፡፡
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ሌሎችም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ኢዜአ ከአሶሳ ዘግቧል፡፡