3ተኛው የኢጋድ አባል ሀገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

141

መጋቢት 21 ቀን 2014 (ኢዜአ) 3ተኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) አባል ሀገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እንዲሁም የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋን ጨምሮ የአባል አገራቱ የትምህርት ሚኒስትሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ጉባኤው አካታች ፣ተደራሽ እና ጥራት ያለው ትምህርት፤ ለስደተኞች፣ከስደት ተመላሾች እንዲሁም ስደተኞችን ተቀብለው እያስተናገዱ ያሉማህበረሰቦች የሚያገኙበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በተጨማሪም በጉባኤው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ታህሳስ  2021 በጅቡቲ ተካሂዶ በነበረው ጉባኤ በቀጣናው በትምህርት ዙሪያ ለመስራት የተያዙ እቅዶችን በሚመለከት ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

በጉባኤው የጅቡቲ፣ኬኒያ፣ሶማሊያ ፣ደቡብ ሱዳን ፣ኡጋንዳ እና የሱዳን ትምህርት ሚኒስትሮች እና የሚኒስትሮች ተወካዮች ተሳታፊ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም