ፖሊስ ዘመናዊ ሰራዊት እንዲሆን የፌደራል መንግሥት ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አረጋግጣለሁ ­- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ

72

መጋቢት 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) ፖሊስ ዘመናዊ ሰራዊት እንዲሆን የጀመርነውን ሪፎርም አጠናክረን የምንቀጥልና የፌደራል መንግሥት ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አረጋግጣለሁ ­ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፖሊስ እንደ ህግ አስከባሪ ህግ ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ እንደ ወንጀል መርማሪ የወንጀል ምርመራ ክህሎት ያለው፣ የስነ-ባህሪ ጥናት ያጠና እንዲሁም ‘ቢሄቪየራል ሳይኮሎጂን ጠንቅቆ የሚያውቅ እንዲሆን የተጀመረው ሪፎርም እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

በተጨማሪም እንደ ሰራዊት ወታደራዊ ብቃት ያለው፣ እንደ አድማ በታኝ የተሟላ ተክለሰውነት ያለው፣ እንደ ደህንነት ተቋም መረጃ መሰብሰብና መተንተን የሚችል፣ ዘመኑን ለመዋጀት ቴክኖሎጂ ብቃትና ግንዛቤ ያለው እንዲሆን የሚሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ፖሊስ ዐሻራ፣ ዲ.ኤን.ኤ. እና ዲጂታል ሲግኔቸር እንዲሁም ዲጂታል ፎረንሲክ መተንተን የሚችል ዘመናዊ ሰራዊት እንዲሆን ለማስቻል የተጀመረው የለውጥ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

ለለውጥ ስራው የፌደራል መንግሥት ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርግም አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም