የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ምክክር ለማድረግ ሐዋሳ ገቡ

83

መጋቢት 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ምክክር ለማድረግ ሐዋሳ ከተማ ገብተዋል።

በክልሉ ባህል ቱሩዝምና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃጎ አገኘውን ጨምሮ ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በቆይታቸውም ከደቡብ እና ከሲዳማ ክልሎች ርዕሰ መስተዳደሮች እና ከሌሎች ዘርፉ ከሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ጋር የቱሪዝም እንቅስቃሴን በቅንጅት ማሳደግ ስለሚቻልበት ሁኔታ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአገር ውስጥ ቱሪዝም፣ በመዳረሻና መስህብ ልማት፣ በቱሪዝም ግብይት እና ፕሮሞሽን ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚደረግም ተጠቁሟል።

የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ማስፋፋት፣ የቱሪስት አገልግሎት ብቃት ማረጋገጥ እና ደረጃ ምደባ እንዲሁም የቱሪዝም መረጃ አያያዝ እና አስተዳደር ጉዳዮችም እንዲሁ የምክክሩ አካል ናቸው።

ከውይይት መርሀ-ግብሩ በተጨማሪም የቱሪዝም ሀብቶች ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም