የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

90


መጋቢት 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ነው፡፡

በ2004 ዓ.ም ትኩረቱን በመካከለኛና ትላልቅ የማምረቻና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ቴክኖሎጂን መጠቀም፣ መቅዳትና ማላመድን መሠረት ያደረገ የሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ በማውጣት የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡

በፖሊሲው አፈጻጸም ሂደት የተገኙ ውጤቶች ቢኖሩም መሰረታዊ ለውጥ ከማምጣት አንፃር ስኬታማ እንዳልነበር ከተደረጉ ጥናቶች መረዳት ተችሏል።

በመሆኑም ለአገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ልማት ልዩ ትኩረት የሚሰጥ፤ የኢንተርፕራይዞችን የቴክኖሎጂ አቅም በማሳደግ ከምርታማነታቸው ጋር ያላቸው ትስስር የሚያጠናክር፤ ለፈጠራ ስራ /Innovation/ ትኩረት የሚሰጥ ፖሊሲ በማስፈለጉ፣ ከግብርና እና ከማኑፋክቸሪንግ በተጨማሪ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና አይሲቲ ለአገራዊ ብልጽግና መሰረት ተደርገው በመወሰዳቸው በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን እንዲታገዙ ማድረግ የሚገባ በመሆኑ፣ በአጠቃላይ ለአዳዲስ ለውጦች እና ፍላጎቶች ምላሽ መስጠት የሚችል እና የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማትን የሚያፋጥን ሁሉአቀፍ ፖሊሲ ማዘጋጀት አስፈላጊ እንደሆነ ታምኖበታል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ በጥልቀት ተወያይቶ ግብዓቶች በማጽደቅ ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡2. ምክር ቤቱ በመቀጠል የተወያየው የ11 የአስፈጻሚ ተቋማትን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረቡ ረቂቅ ደንቦች ላይ ሲሆን በፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 መሰረት፡-

የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን፣
• የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት፣
• የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣
• የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣
• የኢትዮጵያ ደን ልማትን ሥልጣን፣
• የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት፣
• የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት፣
• የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣
• የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት፣
• የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እና
• የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት
አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረቡ ረቂቅ ደንቦች ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል ያጸደቀ ሲሆን ደንቦቹ በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውሉ ምክር ቤቱ ወስኗል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም