የአማራ ክልል ምክር ቤት ሹመቶችን አፀደቀ

110

ባህር ዳር መጋቢት 16/2014 (ኢዜአ ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ።

የአማራ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለና በሌሎች በሚመለከተቸው አካላት የቀረቡ የካቢኔ፣ የዳኞችና የቦርድ አበላትን ሹመት ተቀብሎ በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ።

ተሿሚዎቹ በትምህርት ዝግጅታቸውና በስራ ልምዳቸው የተሻለ ብቃት እንዳላቸው ተብራርቷል።

በዚህ መሰረት፣

  1. አቶ ደሳለኝ ጣሰው የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ
  2. ዶክተር አማረ ብርሃኑ ደግሞ የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ሆነው ተሹመዋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የስራ አመራር ቦርድ መርጧል።

ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉቀን ሰጥየን በአብላጫ ድምፅ ተሹመዋል።

ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የስራ አመራር ቦርድ አቶ ግርማ የሽጥላ ሰብሳቢ

                         ዶክተር አህመዲን መሃመድ አባል

                           ዶክተር ጥላሁን ማህሪ አባል

                            አቶ ግዛቸው ሙሉነህ አባል

                             ዶክተር አለማየው እሸቴ አባል

                            ዶክተር ዳዊት መኮነን አባል

                              አቶ እንግዳ ወርቅ ታደሰ አባል

                            አቶ ተስፋሁን አለምነህ አባል ሆነው በምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ ተሹመዋል።

የቦርድ አባላቱ ሚዲያው ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲቀጥል ሙያዊ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ ይወጣሉ ተብሎ ታምኖባቸዋል።

በተጨማሪም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን አብዮ የቀረቡ 160 የወረዳ እጩ ዳኞች ሹመት ቀርቦ በምክር ቤቱ አባላት ፅድቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም