ነገ በመላው አዲስ አበባ የህዝብ ውይይት ይደረጋል

69

መጋቢት 13/2014(ኢዜአ) ነገ በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ወረዳዎች ፤በክ/ከተማ እንዲሁም በከተማ ደረጃ የህዝብ ውይይቶች እንደሚካሄድ ከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡

በውይይት መድረኩ በየደረጃው ህብረተሰቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎችና ሃሳቦች ይደመጣሉ ለቀጣይ ስራዎችም በግብአትነት እንደሚወሰዱ ተጠቅሷል፡፡

እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ መጠናቀቅን ተከትሎ የጉባኤውን ውሳኔዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ከህዝቡ ጋር የጋራ በማድረግ ለቀጣይ ስራዎች መግባባት ላይ ለመድረስ ያለመ መድረክ መሆኑ ከከንቲባ ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም