ከንቲባ አዳነች አቤቤ የለቡ ሁዋጂያን ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ

60

መጋቢት 13 ቀን 2014 (ኢዜአ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የለቡ ሁዋጂያን ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኢንዱስትሪ ፓርኮች በስራ ዕድል ፈጠራና ውጭ ምንዛሬ የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያመጡ መንግስት አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል::

በተለይም ፓርኮቹ ምን አይነት ችግሮች እየገጠማቸው ነው ፣እንዴት ሊፈታ ይችላል፣ ከመንግሥት ምን ይጠበቃል የሚለው እየተለየ መሆኑን ተናግረዋል::

የዚህ ጉብኝት ዋና ዓላማም ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት መሆኑንም ከንቲባ አዳነች አብራርተዋል::

በጉብኝቱ ላይ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ የመዲናይቱ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል::

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም