ማዕከላዊ ዕዝ ከህዝብ ጋር ያለውን ትስስር ለማጠናከር የሚያስችል የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው

65

ሰቆጣ፣ መጋቢት 11 ቀን 2014 (ኢዜአ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት ማዕከላዊ ዕዝ ከህዝብ ጋር ያለውን ትስስር ለማጠናከር የሚያስችል የምክክር መድረክ በሰቆጣ ከተማ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ፣ የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች እና አባላትን ጨምሮ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የሥራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እየተሳተፉ ነው።

የዕዙ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮሎኔል በዛብህ ይመር ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ምክክሩ ዕዙ የላቀ ህዝባዊነት የተላበሰ የግዳጅ አፈጻጸም እንዲኖረው ለማድረግ ያለመ ነው።

ሠራዊቱ የአካባቢውን ዘላቂ ሰላም በማስጠበቅ የህዝብ ደጀንነቱን የበለጠ ማጠናከር በሚያስችሉት ጉዳዮች ላይ ከህዝቡ ጋር እየመከረ መሆኑን ተናግረዋል።

"የማዕከላዊ ዕዝ ወደ ብሔረሰብ አስተዳደሩ ከመጣ ጊዜ ጀምሮ ሰላምና ደህንነት ከማስጠበቅ ባለፈ የልማት ስራዎች አከናውኗል" ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም