ከንቲባ አዳነች አቤቤ አትክልት ተራ አካባቢ ለሚገነባው የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርያ ማዕከል የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ

63

መጋቢት 11 ቀን 2014 (ኢዜአ)የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አትክልት ተራ አካባቢ ለሚገነባው የእሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡

ከኢኮኖሚ ዕድገት፤ከህብረተሰብ እቅስቃሴ እና የልማት መስፋፋት በተያያዘ የሚያጋጥሙ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ማእከል ለመገንባት ሲሆን ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመሠረት ድንጋይ በዛሬው እለት በማኖር የፕሮጀክቱን ግንባታ በይፋ አስጀምረዋል።

ከንቲባዋ የመሠረት ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅት እንደተናገሩት ሕዝቡ በሚኖርበት አካባቢ ሁሉ የእሳት አደጋ ስጋቶችን በመለየት ለመቀነስ የበኩሉን ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም