የአሜሪካ ወሳኝ አጋር የሆነችው ኢትዮጵያን የሚጎዳውን HR 6600ን ኮንግረሱ በምንም መልኩ መደገፍ የለበትም -ኢትዮጵያን አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል

109

መጋቢት 9 ቀን 2014 (ኢዜአ)የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ወሳኝ አጋር የሆነችው ኢትዮጵያን የሚጎዳውን HR 6600 ረቀቂን ን ኮንግረሱ በምንም መልኩ መደገፍ የለበትም ሲል ኢትዮጵያን አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል አሳሰበ።

የካውንስሉ መሪዎች ከአፕ ስቴት ኒውዮርክ ኮንግረስማን_ጆሴፍ_ሞራለ ቡድን ጋር በተደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

የካውንስሉ ፕሬዝዳንት ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ ለተወካዩ ጆሴፍ ሞራለ ሲናገሩ ግራ የገባን ይሄው ፓርቲ ከካውንስሉ ጋር በመሆን HRes128 ስናሳልፍ ህወሃት በኢትዮጵያ ላይ ያደረገውን መጠነ ሰፊ በድልና ወንጀል በማመዛዘን የደገፋችሁን እና ህጉንም እንዲወጣ የረዳችሁን ባለስልጣናት መልሳችሁ ይህንን የሚያፈርስ ረቂቅ ህግ ስታወጡ እጅግ የሚያሳዝን ነው ብለዋል።

“አሸባሪው ህወሃት ለ27 አመታት ያፈረሳት ሀገር በዘርና በተለያዪ ችግሮች ተውተብትባ ባለችበት ሰኣትና ከዚህ ለምወጣት እየታገለች ባለች የአሜሪካን የአፍሪቃ ቀንድ ወሳኝ አጋር የሆነችውን ሀገር ኢትዮጵያን በማእቀብ ለመምታት የሚደረገው ሩጫ ተገቢና ትክክል ባለመሆኑ ይህንን ወደ ኮንግረስ ለድምፅ ከመጣ እንዲያስቆሙልን እንጠይቃለን” ሲሉ ለኮንግረሱ ተወካይ አስረድተዋል።

እኛ መራጮች የሆነው የኒዎርክና አካባቢው የሲቪክ ካውንስል ኢትዮጵያን አሜሪካውያን መራጮች በዲሞክራት ፓርቲ አካሄድ አዝነናል ሲሉ ያመለከቱት ደግሞ ወይዘሮ ምስራቅ ተስፋዪ ናቸው።

የካውንስሉ አመራር እና የዩኒቲ ፎር ኢትዮጵያ ዴሬክተር አቶ ስዩም አሰፋ በበኩላቸው ኢትዮጵያውያን ከዳር ዳር በዚህ ረቂቅ ህግ አዘነዋል እኛ መራጮች ይህንን ፍላጎታችንን የሚሰማ ወኪል ማግኘት ስለምንፈልግ ይህንን በአስቸኳይ እንድታዩት ምክንያቱም ይህ የካውንስላችን ቀዳሚ አጀንዳና ጥቅም በመሆኑ የተከበሩ ኮንግረስ እርዳታዎትን እንፈልጋለን ብለዋል።

ይህን ጉዳይ እንድከታተለው መጣችሁ ስላናገራችሁኝ እጅግ ደስ ብሎኛል ያሉት የኮንግረሱ ወኪል፣ ቢሯቸው HR6600 የተባለውን ረቂቅ ህግ በጥልቀት እንደሚመረምሩት እና ሴኔት ላይ ያለውን ተመሳሳይ ረቂቅም በማጥናት የካውንስሉን ስጋት በመረዳት አስፈላጊውን እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል።

እኛን ያሳሰበን ይህን ረቂቅ ህግ በማፅደቅ በህዝብ ላይ የሚደርሰው ኢኮኖሚያዊ ችግር በመሆኑ በአስቸኳይ ትብብርዎትን እንፈልጋለን በማለት ማሳሰባቸውን ከካውንስሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም