ኤምባሲው ለዜጎቻችን ደህንነት እየሰራ ነው

84
አዲስ አበባ ነሃሴ 28/2010 በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ በአገሩ በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ ጥቃት እንዳይፈፀም ከአገሪቱ መንግስት ጋር እየሰራ መሆኑን ገለጸ፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት በሶዌቶ ከተማ እና አካባቢው በውጭ አገር ዜጎች ጥቃት ላይ መፈፀሙን ተከትሎ አንድ ኢትዮጵያዊ ህይወቱ ማለፉና ሌላ ዜጋችን ላይ አካል ጉዳት በመድረሱን ለዜጎቻችን ተገቢው የመብት ጥበቃ እንዲካሄድ ኤምባሲው ከደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የፀጥታ መዋቅር ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡ የደቡብ አፍሪካ መንግስትም በስራ ፈቃድም ሆነ በስደተኝነት የሚኖሩ ዜጎቻችንን ሰብዓዊ ክብር እንደሚያስጠብቅ ማረጋገጫ መስጠቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ገልጿል፡፡ በአገሪቱ የሚገኙ ዜጎቻችን ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እየጠየቀ ችግር ሲያጋጥማቸው ደቡብ አፍሪካ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ 0123462947 እና 0123462110 የስልክ ቁጥሮችን በመጠቀም ጥቆማ እንዲሰጡ ጠይቋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም