12 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት ከውጭ እያስገባ ነው - ኢዜአ አማርኛ
12 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት ከውጭ እያስገባ ነው
103
መጋቢት 7 ቀን 2014 (ኢዜአ) መንግስት 12 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት ከውጭ እያስገባ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ገለጸ።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ፤ የምግብ ዘይት ዋጋ ንረትን ለማረጋጋት የሚደረገውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም እጥረቱን ለማቃለልና ገበያውን ለማረጋጋት 12 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት ከውጭ እየገባ መሆኑን ገልጸዋል።
በሚቀጥሉት ሶስት ወራትም 150 ሚሊየን ሊትር ዘይት ከውጭ የሚገባ መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህም በገበያው ላይ የሚስተዋለውን እጥረትና የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
ባለፈው ዓመት 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ሊትር የምግብ ዘይት ከውጭ ገብቶ መሰራጨቱን አስታውሰው፤ ባለፉት ስምንት ወራት 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ሊትር ዘይት በፍራንኮ ባሎታ በኩል ወደ ሀገር ቤት ገብቶ ተሰራጭቷል ብለዋል።