ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን መቀበል ጀመረ

175

መጋቢት 05 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ከፍተኛ ውድመት ተፈፅሞበት ተዘግቶ የቆየው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል።

ጥሪ የተደረገላቸው ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት ጀምረው አስፈላጊው የፍተሻ ስራን በማከናወን ወደ ግቢ በመግባት ላይ መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ መጋቢት 5 እና 6 ቀን 2014 ዓ.ም ለተማሪዎቹ ምዝገባ የሚያካሂድ ሲሆን÷ ለተማሪዎቹም የትራንስፖርት አገልግሎት ማመቻቸቱን አስታውቋል።

በዚሁ መሠረት ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በወልዲያ መናኸሪያ፣ በፒያሳ፣ በአዳጎና ጎንደር በር ፌርማታዎች ላይ በመገኘት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም