የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ጥሩ መሰረት ያስቀመጠ መሆኑን በተግባር ያሳየ ነው

63

አዲስ አበባ መጋቢት 5/2014 /ኢዜአ/ የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት ጥሩ መሰረት ያስቀመጠ መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን በጉባኤው የተጋበዙ ታዛቢዎች ተናገሩ።

ለሶስት ቀናት የተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።

በጉባኤው የፓረቲው ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንቶች፤ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ስራ አስፈፃሚዎች አሳታፊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ መከናወኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው ታዛቢዎች ገልጸዋል።

በጉባኤው የሃሳብ ክርክሮች እየተደረጉ ለአገርና ህዝብ የሚጠቅሙ ውሳኔዎች እየተላለፉ ቀጣይ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውን ተመለክተናል ነው ያሉት።

ከፓርቲ ፕሬዝዳንት እስከ ስራ አስፈፃሚዎች ምርጫ የነበረው ሂደትም አሳታፊ፣ ግልጽና ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ታዝበናል ብለዋል።

በመሆኑም የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት ጥሩ መሰረት የጣለ መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ብልጽግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የዳር ተመልካች የነበሩ ክልሎች አገር በመምራት ሂደት ቀጥተኛ ተሳታፊ በማድረጉም ሊደነቅ ይግባዋል ብለዋል የጉባኤው ታዛቢዎች።

በኢትዮጵያ ጉዳይ ዜጎች ከጫፍ ጫፍ እኩል የፖለቲካ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ምህዳሩን በማስፋት አገራዊ አንድነትንና አብሮነትን እያጠናከረ መሆኑንም በትክክል ተመልክተናል ብለዋል።

በጉባኤው የነበረው የምርጫ ሂደት በቴክኖሎጂ ጭምር የታገዘ፣ ተአማኒ እና አሳታፊ መሆኑንም የጉባኤው ተጋባዦች ተናግረዋል።

የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ 225 ማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም 45 የስራ አስፈፃሚ አመራሮችን በመምረጥ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

በአቋራጭ ለመክበር የሚሞክሩ ሌቦችን መታገልና ለሀግ እንዲቀርቡ ማድረግ የብልፅግና አመራሮችና አባላት ቀዳሚ ተግባር መሆኑም የቀጣይ ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ተቀምጧል

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም