የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ዝግጁ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ዝግጁ ነው
264
ድሬዳዋ መጋቢት 4/2014( ኢዜአ ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት ማንኛውንም ጥቃት በመመከት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ከምን ጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑን የኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሚኒስቴሩ የመከላከያ ሠራዊት የሰው ሀብት አመራር ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀነራል ሃጫሉ ሸለመ እንዳስታወቁት የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኢትዮያን ሉዓላዊነት ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ ሆኖ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል።
ሠራዊቱ ኢትዮጵያን የማፍረስ እኩይ ዓላማ ያነገቡ የውስጥ አሸባሪ ቡድኖችን ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም የሉዓላዊነት ስጋት ለመመከት ዝግጁ መሆኑን አመልክተዋል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሉዓላነቷና ብልፅግናዋ የተረጋገጠ ሀገር ለመገንባት መንግሥት እያደረገ ላለው ሁሉን አቀፍ ጥረት ስኬት አስፈላጊውን ሁሉ መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
መንግሥትና ህዝብ ከድህነትና ኋላቀርነት በመላቀቅ ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና ለመሻገር እየተጉ መሆናቸውን የገለጹት ሌተናል ጀነራል ሃጫሉ "ለዚህም ሠራዊቱ መስዋዕትነት ይከፍላል" ብለዋል።
የውስጥ የጥፋት ቡድኖችና የውጭ ግብረ አበሮቻቸው ጫና የቀጠለ ቢሆንም ሠራዊቱ ፈተናዎችንና ጫናዎችን ተቋቁሞ ጥቃትን በመመከት የሀገርን ሕልውና እና ብልፅግና ለማረጋገጥ ዝግጅት አያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።