ለአፍሪካ የጋራ መገበያያ ገንዘብ መመሥረት ደቡብ አፍሪካ ሙሉ ድጋፏን እንደምትሰጥ አስታወቀች

166

መጋቢት 01 ቀን 2014 (ኢዜአ) ለአፍሪካ አህጉራዊ የንግድ ግብይት ለሚያገለግለው የጋራ መገበያያ ገንዘብ መመሥረት ደቡብ አፍሪካ ሙሉ ድጋፏን እንደምትሰጥ አስታውቃለች።

የደቡብ አፍሪካ የአለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ናሊዲ ፓንዶር የአፍሪካ ማዕከላዊና ኢንቨስትመንት ባንኮች እንዲሁም የአፍሪካ የገንዘብ ድርጅት መቋቋም አንዱ ምክንያት የአህጉሪቷን ንግድ በአንድ የመገበያያ ገንዘብ ለማሳለጥ ነው ብለዋል።

የመገበያያ ገንዘቡ መመስረት እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ በመሆኑ ይህንን ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

ደቡብ አፍሪካም በ1991ዱ የአቡጃ ስምምነት መሰረት የአፍሪካን የንግድ፣ የአገልግሎትና፣ የካፒታል ዝውውሮችን የሚያሳልጡ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ ናት በማለት አስታውቀዋል።

በአፍሪካ ህብረት ስብሰባዎች ላይ ለጋራ መገበያያው ፈጥኖ እውን መሆን የተለያዩ ስራዎችን እንደምትሰራ ነው ያስታወቁት።

የአፍሪካ የገንዘብ ተቋማቱ ለጋራ መገበያያው ወደ ስራ መግባት ጉልህ ድርሻ እንደሚኖራቸው ያሰመሩበት ሚኒስትሯ እነዚህ ተቋማት የአጀንዳ 2063 ፕሮጀክት አካል ናቸውም ማለታቸውን ኒውስ 24 አስነብቧል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም