ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ማረፋቸውን በመስማቴ ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

101

የካቲት 25/2014/ኢዜአ/ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባስተላለፉት የሐዘን መልዕክት አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ማረፋቸውን በመስማቴ ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል።

ተለያይተው የነበሩት ሁለቱ ሲኖዶሶች አንድ እንዲሆኑ ቅዱስነታቸው ወሳኙን ሚና መጫወታቸውን አስታውሳለሁ ነው ያሉት።

ነገሮችን በአርምሞ እየተመለከቱ ሀገራችንን በጸሎት ያግዙ ነበር፣ በዚህ ወቅት እርሳቸውን ማጣት ከባድ ጉዳት ነው፣ ለሁላችንም መጽናናትን እመኛለሁ ሲሉ የሐዘን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም