ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ ተሰጥቷል-የድሬዳዋ አስተዳደር

56

ድሬዳዋ የካቲት 24/2014 /ኢዜአ/ በበጀት አመቱ ስድስት ወራት ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰጠቱን የድሬዳዋ አስተዳደር አስታወቀ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የ3ተኛ የሥራ ዘመን አንደኛ ዓመት መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡

የአስተዳደሩከንቲባ ከድር ጁሃር  ለጉባኤው ባቀረቡት ሪፖርት እንዳስታወቁት  በ2014 በጀት ዓመት ስድስት ወራት   ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 180 ባለሃብቶች ፍቃድ ተሰጥቷቸው እንቅስቃሴ ጀምረዋል፡፡

በወራቶቹ ለኢንቨስትመንት መስክ ትኩረት በመስጠት በተከናወኑ ምቹ ሁኔታዎች የባለሀብቶች ተሳትፎ አበረታች እንደነበር ጠቁመው ለ30 ባለሃብቶች ከቀረጥ ነጻ የሆኑ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ  መደረጉን ጠቅሰዋል።

ባለሀብቶቹከሶስት እስከ አምስት  ዓመት ጊዜ ውስጥ  አስፈላጊውን የግንባታና ሌሎች ሂደቶች አጠናቀው  በየተሰማሩባቸው መስኮች ሙሉ ለሙሉ  ወደ አገልግሎት ሲገቡ ለ14 ሺ 780 ሰዎች ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ እድል እንደሚፈጥሩ አመላክተዋል፡፡

በሌላ በኩል በግማሽ አመቱ ለ12 ሺ 8 00 ሰዎች ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ8 ሺ 630 ሰዎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡

በዘርፉ የዕቅዱን 69 በመቶ  አፈጻጸም ማሳካት መቻሉን ጠቁመው  የሥራ እድል ከተፈጠረላቸው ውስጥ 33 በመቶዎቹ ሴቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በተለይምበማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ለተሰማሩ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የመሸጫና ማምረቻ ቦታዎች ያማመቻቸት እንዲሁም የብድር የአገልግሎትና የገበያ ትስስር የመፍጠር ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል ።

በአስተዳደሩበ2012 በጀት አመት .የነበረው 21 በመቶ የሥራ አጥ ምጣኔ ዘንድሮ ወደ 18 በመቶ ዝቅ ማለቱን  አመልክተዋል

ከንቲባው የአስተዳደሩን በህልውና ዘመቻ ድጋፍና ተጓዳኝ ተግባራት ፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር፣ በከተማ በገጠር በምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ጨምሮ በሌሎችም የተከናወኑ ተግባራትን ለጉባኤው አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል ።

ጉባኤው በከንቲባው በቀረበው  ሪፖርት ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም