የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት ጎንደር ከተማ ሲደርሱ በነዋሪዎች አቀባበል ተደረገላቸው

85
ጎንደር ነሀሴ 27/2010 ከኤርትራ በሰቲት  ሑሞራ በኩል ወደ ሀገር የገቡት የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት  ጎንደር ከተማ  ሲደርሱ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡ አባላቱ አስር ሰዓት ከሰላሳ አካባቢ ጎንደር  ሲደርሱ አቀባበል ያደረጉላቸው የከተማው ነዋሪዎች መሃል ፒያሳ ላይ በመሰባሰብ ነው፡፡ ብዛት ያላቸው የከተማው ወጣቶች ፣ የባጃጅ ሾፌሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች እንኳን ለሀገራችሁ መሬት በሰላም አበቃችሁ በማለት ተቀብለው ሸኝተዋቸዋል። አባላቱ ጉዞቸውን  በመቀጠል  ወደ ባህርዳር ማምራት ጀምረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም