126ኛው የዓድዋ የድል በዓል በሚኒሊክ አደባባይ እየተከበረ ነው

57

የካቲት 23 ቀን 2014 (ኢዜአ) 126ኛው የዓድዋ የድል በዓል በሚኒሊክ አደባባይ በድምቀት እየተከበረ ነው።

በክብረ በዓሉ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ኪነጥበባት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦች በሚኒሊክ ሃውልት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ኪነጥበባት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው፥ በመርሃ ግብሩ ላይ የእንኳን አደረሳቹህ መልዕክት አስተላልፈዋል።በመልዕክታቸውም ይህ ትውልድ በህዳሴ ግድብ ላይ ዳግማዊ የዓድዋ ድልን እያስመዘገበ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም