ጋህነን ለክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጥ እንደሚሰራ አስታወቀ

109

ጋምቤላ የካቲት22/2014 (ኢዜአ) የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋህነን) በክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋጥ እየተደረገ ላለው ሁሉን አቀፍ ጥረት ስኬት በትኩረት እንደሚሰራ አስታወቀ።
የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋህነን) ድርጅታዊ ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ በጋምቤላ ከተማ እያካሄደ ነው።

የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ኦኬሎ ቻክ በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንዳሉት ንቅናቄው በጋምቤላ ክልል ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋጥ እየተደረገ ላለው ሁሉን አቀፍ ጥረት ስኬት በትኩረት ይሰራል።

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል መሰረቱ ሰላም ነው ያሉት ሊቀመንበሩ ንቅናቄው ማንኛውንም ፀረ-ሰላም ድርጊቶችን አምርሮ እንደሚታገል አስታውቀዋል።

በክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እውን በማድረግ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሁሉ ጋህነን የበኩሉን አስተዋፆ ለማበርከት በትጋት እንሚሰራም አረጋግጠዋል።

ጋህነን በዚሁ ዛሬ በሚጠናቀቀው ጉባኤው በንቅናቄው ሪፖርት ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅና አዲስ የማዕከላዊ ኮሚቴና የስራ አስፈጻሚ ምርጫ እንደሚያካሂድም ከድርጊት መረሃ ግብሩ ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም