የብልጽግና ፓርቲ የመሠረታዊ ፓርቲ የቅድመ ጉባዔ ኮንፈረንስ በጋምቤላ ማዕከል ተጀመረ

91

ጋምቤላ፣ የካቲት 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) የብልጽግና ፓርቲ የመሠረታዊ ፓርቲ የቅድመ ጉባዔ ኮንፈረንስ ዛሬ በጋምቤላ ክልል ማዕከል ተጀመረ።

ኮንፈረንሱ በመጀመሪያው የጉባዔ ሰነድ ላይ  እንደሚወያይ ተመላክቷል።

"ከከፍታ ወደ ልዕልና፤ እንቅፋትን እንደ ድልድይ ተጠቅሞ ወደ ዘላቂ ብልጽግና መንደርደር" በሚል መሪ ሃሳብ በሚቀርበው ሰነድ ላይ  የመሰረታዊ አደረጃጀት አባላትና  የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

ኮንፈረንሱ በፓርቲው ያለፉት ዓመታት ጉዞ የተገኙ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ  እንደሚመክርም ይጠበቃል።

በክልሉ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚደረግ የብልጽግና ፓርቲ የጋምቤላ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ላክደር ላክባክ ገልጸዋል።

በክልሉ የሙስናና የብልሹ አሰራር ችግሮችን ለማቃለል የተከናወኑ ስራዎች እንደሚገመገሙ ሃላፊው ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም