ዩኒቨርስቲው ለ11 ምሑራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

80

የካቲት 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ11 ምሑራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ።

አግባብነት ባላቸው የትምህርት ክፍሎች ተመርመሮ፣ በየኮሌጆች አካዳሚክ ጉባዔዎች ተፈትሾ፣ አጥጋቢ በሆነ መልኩ በባለሙያ ተገመግሞ በዩኒቨርስቲው ሴኔት ታይቶ እና ይሁንታ አግኝቶ የቀረበለትን የሙሉ ፕሮፌሰርነት መረጃ የተመለከተው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥራ አመራር ቦርድ ለ11 ምሑራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ማጽደቁን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ዩኒቨርስቲው ፡-1. ዶ/ር ቁምላቸው የሺጥላ

2. ዶ/ር ሽመልስ አሰፋ

3. ዶ/ር መንግስቱ ለገሰ

4. ዶ/ር ጉታ ዘነበ

5. ዶ/ር ፋሲል አሰፋ6. ዶ/ር ጥልዬ ፈይሳ 7. ዶ/ር ብሩክ ላምቢሶ8. ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ 9. ዶ/ር ዘበነ ክፍሌ10. ዶ/ር ተረፈ ደገፋ እና

11. ዶ/ር ንጉሴ ደዬሳን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አፅድቋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሚሰጣቸው ምሑራን በመማር ማስተማሩ፣ በጥናትና ምርምር፣ በዩኒቨርስቲ ውስጥ አገልግሎት እንዲሁም በማህበረሰብ አቀፍና ሙያዊ አገልግሎት በዩኒቨርስቲው ሴኔት ሌጅስሌሽን መሰረት የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ ለተወጡ እና ለዓለም የዕውቀት ስርጸት መዳበር ስኬታማ አበርክቶ ላደረጉ መምህራን እና ተመራማሪዎች መሆኑን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም