የጎልማሶች ትምህርትን ለመደገፍ የሚያስችል የዘርፉ ባለሙያዎች ማህበር ተመሰረተ

87

የካቲት 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) የጎልማሶች ትምህርትን በሚጠበቀው ደረጃ ውጤታማ ለማድረግ እና ለመደገፍ የሚያስችል የዘርፉ ባለሙያዎች ማህበር ተመሰረተ።

ዘርፉን አሁን ካለበት ችግር ለማላቀቅ ያለመ የዘርፉ ባለሙያዎች ማህበር በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት የመመስረቻ ጉባዔ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩም የጎልማሶችና የሕይወት-ዘመን ትምህርት እና ማኅበረሰብ ልማት (ጎሕትማል) ባለሙያዎች ማኅበር በኢትዮጵያ በሚል ስያሜ ማህበሩ ተመስርቷል፡፡

የሙያ ማህበሩ መመስረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ቀርቦ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን የሙያ ማህበሩን በቀጣይ የሚመሩ አመራሮችም ምርጫ መካሄዱ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

በምስረታ ጉባኤው ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዘርፍ የተማረ የሰው ሃይል ለማፍራት በሚደረገው ጥረት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም