የአድዋ ድል የሚከበረው ታሪኩን ለመዘከር ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ አዲስ ታሪክ ለመስራት ነው

115

አዲስ አበባ የካቲት 21/2014 /ኤዜአ  የአድዋ ድል የሚከበረው ያለፈውን ታሪክ ለመዘከር ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ አዲስ ታሪክ ለመስራትም ጭምር መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወርቅነሽ ብሩ ገለጹ፡፡
የዘንድሮው 126ኛው የአድዋ የድል በዓል “አድዋ ለኢትዮጵያዊያን ኅብረት፤ ለአፍሪካ የነጻነት ጮራ” በሚል መሪ ሃሳብ ይከበራል።

በመሆኑም የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላ ጥቁር ህዝቦች አሸናፊነትና የፓን አፍሪካኒዝም መነሻ በመሆኑ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወርቅነሽ ብሩ ተናግረዋል።

የአድዋ ድል የሚከበረው ያለፈውን ታሪክ ለመዘከር ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ አዲስ ታሪክ ለመስራትም ጭምር መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም የአድዋ ዘመን አባትና እናቶች ለአገር ሉዓላዊነትና ለህዝቦች ነጻነት የከፈሉትን ዋጋ በማስታወስ አዲስ ታሪክ ለመስራት ሁላችንም መዘጋጀት አለብን ብለዋል።

የአድዋ ድል “በይቻላል መንፈስ” ድህነታችንን በማስወገድ በባዕዳን እየደረሰብን የሚገኘውን ጫና ለመቋቋም በጋራ ኢትዮጵያን ለማልማት መነሳት አለብን ነው ያሉት።

የአሁኑ ትውልድ በተባበረ ክንድ ወቅቱን የሚዋጅ ትግል በማድረግ የአባቶቹን ውጥን ለማሳካት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

በኢትዮጵያ አገራዊ መግባባት በመፍጠር በሰላም ግንባታ፣ በልማት እና ሌሎችም አገራዊ ፋይዳዎች ዙሪያ እጅ ለእጅ በመያያዝ የምንሰራበት ጊዜው አሁን ነው ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታዋ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም