በምሥራቅ ወለጋ ዞን በመስኖ ልማት ከ3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ተሰበሰበ

89

ነቀምቴ፣ የካቲት 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) በምሥራቅ ወለጋ ዞን ከመጀመሪያ ዙር የበጋ ወራት መስኖ ልማት ከ3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ መሰብሰቡን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ የአዝርዕት ልማትና ጥበቃ ባለሙያ አቶ አበራ በየነ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዞኑ በመጀመሪያ ዙር መስኖ 61 ሺህ 11 ሄክታር መሬት በጓሮ አትክልት፣ በስራስር ተክልና በሌሎች ሰብሎች ለምቷል።

ከለማው መሬት ከ8 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን እስካሁን 3 ሚሊዮን 893 ሺህ 269 ኩንታል ተሰብስቦ ለገበያ እየቀረበ መሆኑን  ተናግረዋል።

የተለያዩ የውሀ አማራጮችን በመጠቀም በባህላዊና በዘመናዊ መንገድ እየተካሄደ ባለው የመስኖ ልማት 120 ሺህ አርሶ አደሮች እየተሳተፉ እንደሆነም ጠቁመዋል።

የመጀመሪያው ዙር የመስኖ ልማት ምርት እስከ መጋቢት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተሰብስቦ እንደሚጠናቀቅ ባለሙያው አስታውቀዋል።

በመስኖ ልማቱ የተሳተፉ አርሶ አደሮች ልማቱ ተጨማሪ ገቢ እያመጣላቸው እንደሆነ ገልጸዋል። 

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም