የሀገር መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ አናብስቶች የሜዳይና የእውቅና ሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት እየተከናወነ ነው

86

ሠመራ፤የካቲት 19/2014 (ኢዜአ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ አናብስቶች የሜዳይና የእውቅና ሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት በአፋር ክልል ሠመራ ከተማ እየተከናወነ ነው።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ በህልውና ዘመቻው ላይ የላቀ ግዳጅ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የሠራዊቱ አባላት የሽልማትና እውቅና እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

የኢፌዲሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር  ሹም ፊልድ-ማርሻል ብርሃኑ ጁላና ምክትል ኤታማዦር ሹሙ  ጄኔራል አበባው ታደሰ እንዲሁም የምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ተሰማ ፣የአፋር ክልል ከፍተኛ አመራሮች ፣ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃርና ሌሎች  ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

የተሸላሚ ቤተሰቦች ፣ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና  ሌሎች እንግዶች መታድመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም