የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተጀመረ
120
የካቲት 19 ቀን 2014 (ኢዜአ) የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬ ተጀምሯል።
ማዕከላዊ ኮሚቴው በተለያዩ ወሳኝ አገራዊ አጀንዳዎችና የፓርቲ ሥራዎች ላይ ተወያይቶ በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከቀናት በፊት ባካሄደው ስብሰባ በወሳኝ አገራዊ አጀንዳዎችና የፓርቲ ሥራዎች ላይ ተወያይቶ በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።