ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለስድስት አንጋፋና ወጣት ተመራማሪዎች የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

64

የካቲት 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ገምግሞ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ለስድስት አንጋፋና ወጣት ተመራማሪዎች የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን የዩኒቨርሲቲው የህዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አለምእሸት ተሾመ ገለጹ።

በዚህም መሰረት፦

1. ለዶክተር ማሽላ ደጀኔ ወልደሚካኤል በዕፅዋት በሽታ ጥናት "ፕላንት ፓቶሎጂ"፣

2. ለዶክተር ዋሱ መሐመድ አሊ በዕፅዋት ዝርያ ማሻሻል "ፕላንት ብሪዲንግ"፣

3. ለዶክተር ንጉሴ ቡሳ ፌዳሳ በ"ባዮኬሚስትሪ እና ፊዚዮሎጂ"፣

4. ለዶክተር አቢ ታደሰ በ"ኢንኦርጋኒክ ኬሚስትሪ"፣

5. ለዶክተር ምትኩ እሸቱ ጉያ በእንስሳት እርባታ እና

6. ለዶክተር ተስፋሕይወት ዘሪሁን በቨተርነሪ ክሊኒካል ፓቶሎጂ (ስነ ደዌ) የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንደተሰጣቸው አቶ አለምእሸት ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም