ሀገር አቀፍ የንባብ ሳምንት በዲላ ከተማ ተጀመረ

226

ዲላ ፤ የካቲት 12/2014 (ኢዜአ) “መጽሐፍት ለእውቀት ገበታ መዛግብትና የመጽሓፍ ቅርሶች ለዘመን ትውስታ“ በሚል መሪ ሀሳብ ሀገር አቀፍ የንባብ ሳምንት በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ መካሄድ ጀመረ ።

መርሃ ግብሩ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጽሐፍ ኤጄንሲ ከደቡብ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮና ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።

ወጣቶች ለንባብና ለምርምር ያላቸውን ክህሎት ለማጎልበት እንዲቻል የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ታስቦ የሚካሄድ የንቅናቄ መድረክ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም የንባብ ባህልን የሚያጎለብት ዝግጅቶችን ጨምሮ የተለያዩ የጽሑፍ ሃብቶችና መዛግብት ትዕይንት፣የመጽሐፍት አውደ ርዕይ፣ ከሪከርድ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ጋር በተያያዘ የፓናል ውይይት እንደሚካሄድ ታውቋል።

የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣አንጋፋ ደራሲያን፣ ሃያሲያና አርቲስቶች በተገኙበት በዚሁ ዝግጅት ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲሁም ከአንደኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ምሁራንና ተማሪዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም