የግራር ቤት ተሃድሶ ሆስፒታልና በውጭ አገር የሚኖሩ በጎ ፈቃደኛ ሴቶች ለመከላከያ ሰራዊት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ

114

የካቲት 11 ቀን 2014 (ኢዜአ) የግራር ቤት ተሃድሶ ሆስፒታልና በውጭ አገር የሚኖሩ በጎ ፈቃደኛ ሴቶች ለመከላከያ ሰራዊት 435 ሺህ ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረጉ።

የሆስፒታሉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የፕሮግራም አስተባባሪ ተሾመ ቱሉ በመከላከያ ምድር ሃይል ግቢ በመገኘት ድጋፉን አስረክበዋል።

በቡታጅራ የሚገኘው ግራር ቤት ተሃድሶ ሆስፒታል ለሰራዊቱ ያደረገው ድጋፍ 300 ሺህ ብር ግምት ያለው መሆኑ ተገልጿል።

በካሊፎርንያ ቤኤሬይ የሚኖሩ በጎ ፈቃደኛ ሴቶች ደግሞ 135 ሺህ ብር ግምት ያለው የሴቶች የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

May be an image of 1 person

ሴቶቹ ያደረጉትን ድጋፍም በተወካያቸው ወይዘሮ ገነት አበበ በኩል አስረክበዋል።

የመከላከያ ፋይናንስ ስራ አመራር ዘርፍ ተወካይ ብርጋዴል ጀነራል ዘላለም ፈተና ሁለቱ አካላት ያደረጉትን ድጋፍ በመረከብ ለለጋሾቹም ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም