አንዲት እናት ሶስት ልጆችን በሰላም ተገላገለች

71

ሶዶ፤ የካቲት 10/2014 (ኢዜአ) በወላይታ ዞን ቦዲቲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንዲት እናት ሶስት ወንድ ልጆችን በሰላም ተገላገለች።

የሆስፒታሉ  ስራ አስኪያጅ ዶክተር ወልዴ ቡቃቶ፤ እናቲት በሆስፒታሉ በቂ የቅድመ ወሊድ ህክምና ክትትል ስታደርግ እንደቆየች ገልጸዋል።

በዚህም ዛሬ  ረፋዱ ሶስት ሰዓት ተኩል አካባቢ ሶስት ልጆች በሰላም መገላገሏን አስታውቀዋል።

ወላዷ በሰላም እንድትገላገል የህክምና ባለሙያዎች ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል ።

ህፃናቱ የጤና ሁኔታቸው አሳሳቢ ባይሆንም ከኪሎ በታች በመሆናቸው ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለተሻለ ህክምና መወሰዳቸውን ጠቁመዋል።

በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ የጊዶ ቦዲቲ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወይዘሮ  ብርሃነሽ ቆልቻ  ከዚህ በፊት ሶስት ሴት ልጆች እንዳሏት ለማወቅ ተችሏል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም