ባንኩ በ2013 ዓ.ም ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች ሽልማት ሰጠ

70

የካቲት 08 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2013 ዓ.ም በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች ሽልማት ሰጠ።

ባንኩ ባለፈው ዓመት በተካሄዱ የአትሌቲክስ፣ እግርኳስና የጠረጴዛ ቴንስ ውድድሮች በድምሩ 28 ዋንጫ ማንሳት ችሏል።

ለዚህ ውጤት መገኘት አስተዋጽኦ ለመበራቸው ስፖርተኞች በዛሬው እለት ሽልማት ተበርክቷል።

እንደየደረጃቸው ውጤት ላመጡ ስፖርተኞች ከ1 ሺህ እስከ 80 ሺህ የገንዘብ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንትና የስፖርት ማህበር የበላይ ጠባቂ አቤ ሳኖ፤ በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ እንዳሉት ክለቡ ተወዳዳሪና ውጤታማ የሚባል ነው ብለዋል።

በተለይ በሴቶች ስኬታማ ስፖርተኞችን እያፈራ መሆኑን ጠቅሰው በወንዶች ደግሞ የበለጠ ውጤት ለማምጣት መስራት አለባቸው ብለዋል።

''በሚወዳደሩባቸው ስፖርቶች ሁሉ የአሸናፊነት ወኔ ይዘው መግባት ይገባል'' ያሉት ፕሬዝዳንቱ ለዚህ ግን በቂ ዝግጅትና የረጅም ጊዜ ህልም ይጠይቃል ነው ያሉት።

በክለቡ ቆይታቸው አቅማቸውን እያጎለበቱ የማይሻሻሉ ስፖርተኞችን ይዘን ለመቀጠል እንቸገራለን ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም