ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በኡጋንዳ በተከበረው 41ኛው የሰራዊት በዓል ላይ ታደሙ

93

የካቲት 05 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በኡጋንዳ በተከበረው 41ኛው የሰራዊት ቀን ላይ በመገኘት በዓሉን ታድመዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ በዚህ በዓል ላይ የተገኙት የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ባደረጉላቸው የክብር ግብዣ ነው።

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ፣ "ጥሪያችንን አክብራችሁ በመገኘታችሁ አመሠግናለሁ" ሲሉ ገልጸው፤ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላን እንኳን ደስ አለዎት ብለዋቸዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑም በፕሬዝዳንቱ ለተደረገላቸው ልባዊ አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ በዝግጅቱ ላይ ከተገኙ ከዩጋንዳ፣ ከቡሩንዲ፣ ከሞዛምቢክ እና ከደቡብ ሱዳን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሞች እንዲሁም ከሩዋንዳ፣ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ከኬንያ ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሞች ጋር በተናጠል ተገናኝተው መክረዋል።የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ለየሀገራቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሞች ያስረዱት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በቀጣይ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር እና በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

በዝግጅቱ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያን በመወከል ችግኝ መትከላቸውን ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም