ኦሮሚያና ጋምቤላ ክልሎች በሰላምና በልማት ዙሪያ በትብብር ለመስራት ስምምነት አደረጉ

74

ጋምቤላ፣ የካቲት 04 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኦሮሚያና ጋምቤላ ክልሎች በመጭዎቹ አምስት አመታት በሰላምና በልማት ዙሪያ በጋራ ለሚያከናውኗቸው ተግባራት የትብብር ስምምነት ፊርማ ተፈራረሙ።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦሞድ ኡጁሉ የስምምነት ሰነዱን ፈርመዋል።

ስምምነቱ በክልሎቹ መካከል ካለፉት ሶስት አመታት ወዲህ እየተደረገ ያለውን የሰላምና የልማት ትብብር አጠናክሮ ለማስቀጠል አላማ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጋምቤላ ከተማ በ79 ሚሊዮን ብር ለሚያስገነባው የኢፋ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ የመሰረተ ድንጋይ የሁለቱ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች አስቀምጠዋል።

በወቅቱም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ ትምህርት ቤቱን መገንባት ያስፈለገው የሁለቱን ክልሎች ህዝቦች የትምህርት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

በኦሮሚያና ጋምቤላ ክልሎች መካከል ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ በልማት የሚደረግ ትብብር እየተጠናከረ መጥቷል" ያሉት ደግሞ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ናቸው።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም