የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ጋምቤላ ከተማ ገቡ

123

የካቲት 04 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ዛሬ ጋምቤላ ከተማ ገቡ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ጋምቤላ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በሚኖራቸው ቆይታ በሁለቱ ክልሎች የሁለትዮሽ የሰላምና የልማት ትብብር ዙሪያ ውይይት እንደሚያደረጉ ይጠበቃል።

May be an image of 8 people, people standing and outdoors
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም