በ12ኛው ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር አዲስ አበባ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ይጫወታሉ

73

 አዲስ አበባ የካቲት 3/2014 /ኢዜአ/ በ12ኛው ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር አዲስ አበባ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ከቀኑ 10፡00 ይጫወታሉ
በፕሪሚየር ሊጉ ትናንት በተካሄዱ ጨዋታዎች ሀድያ ሆሳዕና ሰበታ ከተማን ሲያሸንፍ ፋሲል ከነማ ከአዳማ ነጥብ ተጋርቷል።

በ12ኛው ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር ትናንት ከቀኑ 10፡00 ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 ተለያይተዋል።

በጨዋታው አዳማ በአሜ መሀመድ 30ኛው ደቂቃ ቀዳሚ ቢሆንም ኦኪኪ አፎላቢ ለፋሲል ከተማ  74ኛው ደቂቃ ላይ ጎል በማስቆጠር አቻ መሆን ችሏል።

በዚህ ጨዋታ ፋሲል ከነማ አቻ መለያየቱን ተከትሎ የሊጉ መሪ መሆን የሚችልበትን አድል አምክኗል።

ከዚህ ጨዋታ ቀጥሎ ምሽት 1፡00 ላይ በተካሄደው የሃድያ ሆሳዕና እና ሰበታ ከተማ ጨዋታ በሃዲያ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ሀድያ ሆሳዕና በሳምሶን ጥላሁን ብቸኛ ጎል ሰበታ ከተማን 1 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።

12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው የሚደረጉ ሲሆን አዲስ አበባ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ቀን 10፡00 ይጫወታሉ።

ምሽት 1፡00 ሰዓት ላይ ደግም በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 10ኛ ላይ የሚገኘው ባህርዳር ከተማ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠው  ሀዋሳ ከተማ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ፕሪሚሪ ሊጉን  ቅዱስ ጊዮርጊስ በ23 ነጥብ፣ ፋሲል ከነማ በ22 ነጥብ እና  ሀዋሳ ከተማ በ20 ነጥብ እንደየቅደም ተከተላቸው ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

በሊጉ ወራጅ ቀጠና ጅማ አባጅፋር እና ሰበታ ከተማ በእኩል7 ነጥብ የሊጉ ግርጌ 16ኛ እና 15ኛ ደረጃ እንደ ቅደም ተከተላቸው የተቀመጡ ሲሆን አዲስ አበባ ከተማ በ11 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም