በአሸባሪው ህወሃት የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተጀመረ

50

የካቲት 03 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአሸባሪው ህወሃት የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የፅሁፍ መልእክት እና በባንክ አካውንት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተጀመረ።

የትምህርት ሚኒስቴር ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በአሸባሪው ህወሃት ውድመት የደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማት መልሶ ለመገንባት የሚያስችለውን የገቢ ማሰባስቢያ በተመለከተ የጋራ ሥምምነት አደረገ።

በሥምምነቱ መሰረት በ"9222" ላይ ቴሌ ብርን ጨምሮ ማንኛውም አካል ከአንድ ብር ጀምሮ አጭር የፅሁፍ መልእክት በስልክ በመላክ ድጋፋቸውን ማድረግ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000448700945 አካውንት በመጠቀም ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻል ተገልጿል።

አሸባሪው ህወሃት በአማራና አፋር ክልሎች በወረራ በቆየባቸው አጋጣሚዎች በድምሩ 1 ሺህ 90 የትምህርት ተቋማት ሙሉ በሙሉ ሲወድሙ ሶስት ዩኒቨርሲትዎችና ሶስት ኮሌጆችም ተመሳሳይ እጣ ገጥሟቸዋል።

በመሆኑም የትምህርት ተቋማቱን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ሁሉም ድጋፉን እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

የትምህርት ግብቶችን ድጋፍ ለማድረግ የሚፈልጉ አካላት ደግሞ በትምህርት ሚኒስቴር ዋናው ቢሮ በመገኘት ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

የገቢ ማሰባሰቢያው "ኑ የወደመውን የትውልድ ማረፊያ ተቋም አብረን እንገንባ" በሚል መሪ ኃሳብ ነው የሚካሄደው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም