የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ሥልጠና ዛሬ ተጀመረ

124

የካቲት 01 ቀን 2014 (ኢዜአ) የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ መድረክ ሥልጠና ተጀምሯል፡፡

የአቅም ግንባታ መድረኩ ዓላማ አመራሩ ወቅቱ የሚጠይቀውን የአመራር ብቃትና አስተሳሰብ እንዲያጎለብትና የመረጠውን ህዝብ በትጋትና በቅንነት እንዲያገለግል ለማስቻል ነው ተብሏል።

መድረኩ ጥንካሬዎችንና መልካም አፈጻጸሞችን አጠናክሮ በማስቀጠል የታዩ ውስንነቶችን ደግም ነቅሶ በማረም ህዝቡ በሚጠብቀው ደረጃ ለማገልገል የሚያስችል የአመራር አቅም ለማጎልበት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል።

ለሚቀጥሉት አራት ቀናት በሚካሔደው በዚህ የአቅም ግንባታ መድረክ ላይ ከ320 በላይ አመራሮች ሚንስትሮችና ሚንስትር ዴኤታዎችን ጨምሮ የተለያዩ የፌደራል ተቋማት ሀላፊዎችና ምክትል ሀላፊዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም