ኢትዮጵያ ሁሉም ሊያየው የሚገባ የካበተ ታሪክ እና እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ያላት አስደናቂ አገር ነች"

73

ጥር 30 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ ሁሉም ሊያየው የሚገባ የካበተ ታሪክ እና እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ያላት አስደናቂ አገር መሆኗን የኤስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲፖ ድላሚኒ ተናገሩ።

የኤስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲፖ ድላሚኒ በዛሬው እለት የእንጦጦ ፓርክን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጉብኝታቸው በኋላ፤ ኢትዮጵያ ሁሉም ሊያየው የሚገባ የካበተ ታሪክ እና እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ያላት አስደናቂ አገር መሆኗን ገልጸዋል።

ከ20 ዓመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አሁን ላይ የአገሪቱ ብሎም የከተማዋ ነባራዊ ሁኔታ በእጂጉ ተቀይሯል ብለዋል።

በተለይም በከተማዋ ያለው ፈጣን የልማት እና የእድገት ሁኔታ የሚያስደንቅ ሲሆን ለሌሎች አገራትም ጥሩ ተሞክሮ የሚሆን ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ስላሏት አስደናቂ የተፈጥሮና ታሪካዊ ሃብቶች ለሌሎች እንደሚያስረዱም ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ስለ ኢትዮጵያ ይሰሙት የነበረውን በአካል ተገኝተው ለመመልከትና ለመጎብኘት መቻላቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸው ሌሎችም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲያዩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኤስዋቲኒ በቀድሞ ስሟ ስዋዚላንድ በሚል መጠሪያ ትታወቅ የነበረች አገር ስትሆን በንጉሳዊ ሥርዓትም ትተዳደራለች።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም