የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል የአፍሪካ ህብረትን ሊቀመንበርነትን ተረከቡ

117

ጥር 28 ቀን 2014 (ኢዜአ) የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል የአፍሪካ ህብረትን በሊቀመንበርነት የመምራት ሃላፊነቱን ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ሺሴኬዲ ተረከቡ።

35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።

የህብረቱ የወቅቱን ሊቀመንበርነት የተረከቡት የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል የሴኔጋል አራተኛው ፕሬዚዳንት ሲሆኑ እ.አ.አ ከ2012 ጀምሮ እያገለገሉ ይገኛሉ።

ፕሬዚዳንቱ እ.አ.አ በ2019 በተካሄደ ምርጫ አሸንፈው ዳግም መመረጣቸው ይታወቃል።

ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል እ.አ.አ ከ2004 እስከ 2007 ድረስ አገራቸውን በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም