የአፍሪካ ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ በትክክል ሊደመጥ ይገባል

80

ጥር 28 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአፍሪካ ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ በትክክል ሊደመጥ ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህን ወቅት፤ አፍሪካ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ በተገቢው መልኩ እየተወከለች አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከተመሰረተ ከ75 ዓመታት በላይ ባስቆጠረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አፍሪካ ተገቢ ውክልና እንደሌላት ጠቅሰው፤ "ድርጅቱን ሪፎርም ለማድረግ ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው" ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ሌሎች የዓለም አቀፍ ተቋማትም አፍሪካን ማዕከል ያደረገ ለውጥ ሊያደርጉ እንደሚገባም ነው ያነሱት፡፡

በመሆኑም የአፍሪካዊያን ድምጽ በዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ በትክክል ሊደመጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ለጉዳዩ እውን መሆን ደግሞ አፍሪካዊያን ያለምንም ልዩነት በጋራ ሊታገሉ እንደሚገባም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም