የማላዊ ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ አዲስ አበባ ገቡ

51

ጥር 26 ቀን 2014 (ኢዜአ) የማላዊ ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ አዲስአበባ ሲገቡ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

35ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ "የአፍሪካ አህጉርን የስርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፤ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን ያፋጥናል'' በሚል መሪ ሃሳብ በመጪው ቅዳሜና እሁድ ይካሄዳል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም