ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቱኒዚያ፣ ሞሮኮና ኮሞሮስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ

68

ጥር 26 ቀን 2014 (ኢዜአ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቱኒዚያ፣ ሞሮኮና ኮሞሮስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ።

ከ40ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በሁለትዮሽና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለት ከቱኒዚያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦትማን ጄራንዴ ጋር በተመሳሳይ በሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተነጋግረዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሞሮኮ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናስር ቡሪታ ጋር በነበራቸው ቆይታም ኢትዮጵያ በግብርና እና ቱሪዝም ዘርፎች ከሞሮኮ ጋር ጠንካራ ትብብር ማድረግ እንደምትፈልግ ገልጸዋል።

በውይይታቸውም ከግብርና እና ቱሪዝም ዘርፎች በተጨማሪ በሁለትዮሽ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ መክረዋል።

በተመሳሳይም ከኮሞሮስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶይሂር ዱከማል ጋር በሁለትዮሽና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም