የሀረሪ ክልል በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች 7 ሚሊየን ብር የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ

85

ጥር 25 ቀን 2014 (ኢዜአ)የሀረሪ ክልል መንግስትና ህዝብ አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል 7 ሚሊየን ብር የሚገመት የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙኽታር ሳሊህ ለደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጀማል አህመድ አስረክበዋል።

የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙኽታር ሳሊህ በአሁኑ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለማለፍ ትብብርና መደጋገፍ ወሳኝ በመሆኑ ክልሉ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

5 ሚሊየን ብር የገንዘብ እና 2 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ ማድረጋቸውን የተናገሩት ሃላፊው በቀጣይ ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ጀማል አህመድ የክልሉ ህዝብና መንግስት ላደረገው ድጋፍ ማመስገናቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም