ጎባ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ

141

ጥር 24 ቀን 2014 (ኢዜአ) በባሌ ዞን ጎባ ወረዳ በደረሰው የተሽከርካሪ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጎባ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ።

አደጋው የደረሰው በጎባ ወረዳ ልዩ ስሙ ገንዳ ሪራ በተባለ ሥፍራ መሆኑን በጎባ ፖሊስ የሰላም ማረጋገጥ ዲቪዥን ረዳት ኢንስፔክተር ሙክታር ሁሴን ተናግረዋል።

አደጋው ከደሎ መና ወደ ሮቤ ዶዘር እየጎተተ ሲጓዝ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ክሬን ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ከሮቤ ወደ ደሎ መና በመጓዝ ላይ ከነበረው የፖሊስ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው ብለዋል።

በደረሰው የተሽከርካሪ አደጋ ዘጠኝ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ህይወት ሲያልፍ ፥ በአራቱ ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱም ተገልጿል።

በአደጋው ክሬኑን ሲያሽከረክር የነበረው ረዳት በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ረዳት ኢንስፔክተር ሙክታር ተናግረዋል።

አደጋው የደረሰው በትናንትናው ዕለት ከቀኑ 9:00 ሰዓት ገደማ ሲሆን ፥ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ብለዋል።

ከባድና ቀላል አደጋ የደረሰባቸው የፖሊስ አባላት ጎባ ሪፌራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም