የውጭ ምንዛሬን ከሚያስገኙ አገልግሎቶች 74 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል

76

ጥር 23 ቀን 2014 (ኢዜአ)  ባለፉት ስድስት ወራት የውጭ ምንዛሬን ከሚያስገኙ አገልግሎቶች 74 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።

ኩባንያው ባለፉት ስድስት ወራት በጦርነቱ ምክንያት 4 ቢሊየን ብር ማጣቱንም ተገልጿል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ በሰጡት መግለጫ የኩባንያውን የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም አበረታች ነው።

በተለይም የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች 74 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገልጸዋል።

ይህም የእቅዱን 89 ነጥብ 3 በመቶ ያሳካ መሆኑን ጠቁመው በቴሌኮም አገልግሎትም ኩባንያው 28 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል የአራተኛው ትውልድ የኔትወርክ አገልግሎትን 136 ለሚሆኑ ከተሞች ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል።

ከቴሌ ብር አገልግሎት ጋር በተያያዘ ወደ ሥራ ከገባ ጊዜ ጀምሮ የ5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ግብይት መፈጸሙን ተናግረዋል።

የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ቁጥርም 13 ነጥብ 1 ሚሊዮን መድረሱን በመጠቆም።

በቴሌኮም መሰረተ ልማት ላይ ባለፉት ስድስት ወራት 10 በሚሆኑ ሪጅኖች ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከፍ ያለ ጉዳት እንደደረሰባቸው አመላክተዋል።

በዚህም ኩባንያው በመሰረተ ልማቶቹ ላይ በደረሰው ጉዳት 4 ቢሊዮን ብር ማጣቱን ተናግረዋል።

በመሰረተ ልማቶቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት በመጠገን በቅድሚያ ለኅብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን አገልግሎት እንዲጀምሩ መደረጉንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም