ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ ወደ ሳውዲ አቀኑ

81
አዲስ አበባ ግንቦት 9/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ ለይፋ የስራ ጉብኝት ወደ ሳውዲ ዓረቢያ አቀኑ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱን የሚያደርጉት የአገሪቷ ንጉስ ቢን ሳልማን አብዱልአዚዝ ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት ነው፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ በሚያደርጉት የመጀመሪያ ጉብኝታቸው ከአገሪቷ ባለስልጠናት ጋር በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ በተመረጡበት ወቅት የደስታ መግለጫ ከላኩ አገሮች መካከል ሳውዲ ዓረቢያ በቀዳሚነት ተቀምጣለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀደም ሲል በጅቡቲ፣ ሱዳን እና ኬንያ ጉብኝት ማድረገቸው ይታወሳል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም